Seattle Public Schools

Resources

Health Services

የአዲሱየትምህርትዓመትአስፈላጊየጤናመረጃ

ክትባቶችዎ ወቅታዊ ናቸው?

የዋሽንግተን ስቴት ህግ እያንዳንዱ ተማሪ ትምህርቱን ለመከታተል የሚያስፈልጉ የክትባት መስፈርቶችን ማክበሩን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ይጠይቃል። ተማሪዎ ለትምህርት ቤት ስለሚያስፈልገው ክትባቶች ከጤና አገልግሎት ደብዳቤ ከደረሰዎ፣እባክዎን ተማሪዎ በደብዳቤው ላይ የተዘረዘሩትን ክትባቶች እንዲወስድ ያድርጉ ወይም ተማሪዎ ከክትባት ነፃ መሆንን የሚያመለክቱ ሰነዶች ያቅርቡ።

የክትባት መዝገቡን ለትምህርት ቤቱ ነርስ ይላኩ ወይም የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ መዝገቡን ወደ ነርስ ፋክስ እንዲያደርገው ይጠይቁ።

የክትባት መስፈርቶች በየጤና አገልግሎት የክትባቶች ድረ ገጽ(Health Services Immunizations page) ላይ ይገኛሉ

ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና ሁኔታዎች

ተማሪዎ ለሕይወት አስጊ የሆነ የጤና ሁኔታ ካለበት (የስኳር በሽታ፣አለርጂ፣የሚጥል በሽታ(Seizure disorder)፣አስም፣ወዘተ)፣የሚከተሉት ዕቃዎች በትምህርት የመጀመሪያ ቀን ወይም ከዚያ በፊት መቅረብ አለባቸው:

  • ሕይወት አድን መድኃኒት
  • የመድሃኒት ፈቃድ ቅጾች
  • የሕክምና አቅርቦቶች

የዋሽንግተን ስቴት ህግ በትምህርት ቀን የተማሪዎን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ፣እነዚህ እቃዎች በትምህርት ቤቱ ነርስ እስኪቀበሉ ድረስ ተማሪዎ ከትምህርት ቤት እንዲገለል ይደነግጋል።እባኮትን እነዚህን እቃዎች ለማቅረብ ማንኛውም አይነት መሰናክሎች ካሉዎት ለትምህርት ቤትዎ ነርስ ያሳውቁ።ነርሶች ድጋፍ ሊሰጡ ይችላሉ። የማግለል ሂደቱን በተመለከተ የSPS ፖሊሲ 3413(SPS Policy 3413) በትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች እና ሂደቶች ገጽ ላይ “የተማሪ ክትባት እና ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና ሁኔታዎች” በሚለው ስር ይገኛል።”

የጤና ዝማኔዎች

እባክዎን ልጅዎ በደህንነቱ እና በትምህርቱ ላይ ተጽእኖ ሊያመጣ የሚችል ማንኛውንም የጤና ችግር ለትምህርት ቤቱ ነርስ ያሳውቁ።

አመታዊ የተማሪ ጤና ዝማኔ(Annual Student Health Update)ቅጽ ይሙሉ:

የመድሃኒት ቅጽ

በትምህርት ቤት የሚወሰዱ መድኃኒቶች ፈቃድ(Authorization for Medications Taken at School) ለመሙላት የጤና አቅራቢዎን ይጠይቁ

  • እያንዳንዱ መድሃኒት የራሱ የሆነ ቅጽ ያስፈልገዋል
  • የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ መፈረም አለበት
  • እርስዎ በቅጹ ላይ መፈረም አለቦት

 ይህ ለሁሉም መድሃኒቶች ያስፈልጋል።

መድሃኒት

ሁሉም መድሃኒቶች በዋናው መያዣቸው እና በተማሪው ስም የተፃፉ መሆን አለባቸው።በሐኪም የታዘዘ መድኃኒት የፋርማሲ መለያ ሊኖረው ይገባል።

የድንገተኛ ጊዜ መድሃኒቶች በትምህርት የመጀመሪያ ቀን ወይም ከዚያ በፊት በትምህርት ቤቱ ህንፃ ውስጥ መኖር አለባቸው።

የመድኃኒት ማብቂያ ቀናትን ያረጋግጡ!ሙሉውን የትምህርት አመት የሚቆዩ መድሃኒቶችን ለማግኘት ይሞክሩ።

የፍሉ ክትባቶች ህይወትን ለማዳን ይረዳሉ!

ለተማሪዎ እና ለቤተሰብዎ አባላት የፍሉ ክትባት ለመውሰድ ቀጠሮ ያስይዙ። እንዴት እንደሆነ እነሆ፡

  • የትምህርት ቤት የጤና ማእከል ያነጋግሩ (ተማሪዎች ብቻ)
  • ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ እንክብካቤን ይጠይቁ

ስለወደፊት ማስታወቂያዎች የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ድህረ ገጽ(Seattle Public Schools website ይመልክቱ።

የመተንፈሻ አካላት በሽታ ይከላከሉ

ኮቪድ-19ን ጨምሮ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ስርጭት ለመቆጣጠር እና የእርስ በርስ ደህንነትን ለመጠበቅ እርምጃዎችን ይውሰዱ።

  • ክትባት ይውሰዱ(Get vaccinated)
  •  ህመም ከተሰማዎት ቤት ይቆዩ
  • የኮቪድ-19 ምልክቶች ካለብዎ ይመርመሩ(Get tested)
  • እጅዎን በተደጋጋሚ ይታጠቡ
  • እጆችን ከፊትዎ ያርቁ

ተማሪዎ በት/ቤት ላይ ለተመሰረተ የጤና ጣቢያ ያስመዝግቡ!

ተማሪዎ በዲስትሪክቱ ውስጥ ወደ ማንኛውም የትምህርት ቤት ጤና ጣቢያ መሄድ ይችላል።እባክዎ አስቀድመው ይደውሉ።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የትምህርት ቤት ጤና ጣቢያ ይፈልጉ(Locate a School Based Health Center near you) ወይም ለእርስዎ ቅርብ የሆነውን ለማግኘት ይህንን ካርታ (interactive map)ይጠቀሙ።